top of page

Arts

አዎ ዐማራ ነኝ !
--በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተገጠመ--

የሚያነጋግረን ብዙ የሚያስጨንቀን ፣
ሌላ ተግባር ጠፍቶ ባገር የሚከወን ፣
የእድገት ደረጃችን የደረስንበቱ ፣
መሸንሸን ከሆነ ዝርያን ባይነቱ !

ተፈጥሮ ያደለችኝ ፣
መርቃ የሰጠችኝ ፣
ከስር ከመሰረቱ ፣
ከጠዋት ከጥንቱ ፣
ያዳም የሔዋን ዘር ህልውና ያለኝ ፣
በእኔነቴ የማምን አዎን ዐማራ ነኝ !

የዋህ ሆደ ቡቡ ሁሉን አሳዳሪ ከሁሉ አዳሪ ፣
ልበ ሙሉ ቆራጥ በቁም ነገር ኗሪ ፣
በራሴ እምታመን ባገሬ የምኮራ ፣
ለሀቅ የምታገል ላገሬ እምሰራ ፣
ሸፍጥና ክደት ባንዳነት ያልበገረኝ ፣
የነፃሁ የጠራሁ አዎን ዐማራ ነኝ !

የሀገሬን ክብር ታሪኬን የማልሸጥ ፣
ዘመድ ወገኖቼን በብር የማልለውጥ ፣
እማልንበረከክ ለነጭ ፍርፋሪ ፣
ጉበኛ ያይደለሁ ትውልድ አሳፋሪ ፣
ጀግንነት አመሌ ወኔ ያልተለየኝ ፣
ተጠየቅ ካላችሁ አዎን ዐማራ ነኝ።


 

Negere-Amhara is a space dedicated to keeping this website's visitors informed on historical and current developments surrounding the people of Amhara. 

  • White Facebook Icon
bottom of page